img

በአብዛኛው የሀሞት ጠጠር ምንም አይነት ምልክት የሉትም ፡ ምልክቶች ከሌሉት ደግሞ ምንም አይነት ህክምና አይፈልግም ፡ አንዳንድ ታካሚዎች ግን የሚከተሉት ምልክቶች ሊኖራቸው ይችላል ፡

በአብዛኛው የሀሞት ጠጠር ምንም አይነት ምልክት የሉትም ፡ ምልክቶች ከሌሉት ደግሞ ምንም አይነት ህክምና አይፈልግም ፡ አንዳንድ ታካሚዎች ግን የሚከተሉት ምልክቶች ሊኖራቸው ይችላል ፡ 

1. የቀኝ የላይኛው የሆድ ክፍል ህመም
2. የሆድ መነፋት የምግብ አለመፈጨት ስሜት 
3. ተደጋጋሚ የማቅለሽለሽ እና የማስመለስ 
4. በጣም አልፎ አልፎ የሚከሰት የሀሞት መስመር በጠጠር መዘጋት (ይህ የአይን ቢጫ መሆን ሊያመጣ ይችላል

የትኞቹ ታካሚዎች የቀዶ ህክምና ይፈልጋሉ?

1. ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች ካሉባቸው
2. የሀሞት ከረጢት ኢንፌክሽን ወይም መቆጣት ከተከሰተ እና በምርመራ መኖሩ ከተረጋገጠ
3.የአይን ቢጫ መሆን ካመጣ 
4. የቆሽት ማስቆጣት (Pancreatitis) ካስከሰተ