img

RH negative እናቶች ባለቤታቸው RH positive ከሆነ RH positive ልጅ ይወልዳሉ። አንድ እናት RH positive የሆነ ልጅ ከወለደች ...

RH negative እናቶች ባለቤታቸው RH positive ከሆነ RH positive ልጅ ይወልዳሉ። አንድ እናት RH positive የሆነ ልጅ ከወለደች ወይም በማንኛውም ምክንያት RH positive ደም ከወሰደች ለቀጣይ እርግዝናዎች የፅንሱን ቀይ የደም ሴሎች ሊጎዱ የሚችሉ ቀመሞችን ታመነጭና ቀጣይ ፅንሶች በማህፀን ውስጥ እያሉ  ደም ማነስ፣ ቢጫ መሆን፣ እና የጉበት ችግር ሊገጥመው ይችላል። ይህ ሲሆን 
1- የመጀመሪያው ፅንስ ምንም ችግር አይገጥመውም። 
2- ቀጣይ እርግዝናዎች ላይ ከላይ የተጠቀሰው ችግር ይገጥማቸዋል። እናም የፅንሱ ጤናና ህይወት አደጋ ይገጥመዋል። 


ይህ እንዳይከሰት ምን ማድረግ ይቻላል? 
ይህንን ለመከላከል እናትየው RH Ig የሚባል መርፌ መወጋት ይኖርባታል።  እናቶች ይህንን መርፌ መወጋት ያለባቸው 
1- በእርግዝና ወቅት በ28ኛው ሳምንት እና እንደወለደች በ72 ሰአት ውስጥ
2- ውርጃ ከተከሰተ፣ ከማህፀን ውጪ እርግዝና ከተፈጠረ፣ በእርግዝና ወቅት በማንኛውም ምክንያት ደም ከፈሰሳት 
3-  በማንኛቸውም ወቅት አስገዳጅ በሆነ ምክንያት RH positive ደም ከወሰደች መርፌውን መወጋት አለባት። 


ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት እናት ለRH positive ከተጋለጠችና መርፌውን ካልወሰች እርግዝና ቢከሰት ምን ማድረግ ይቻላል? 
1- የፅንሱ ጤና ቢያንስ በአልትራሳውንድ ጤንነቱን ክትትል ማድረግ 
2- ፅንሱ አነስተኛ ደም ማነስ ካለው ምጥ እስከሚመጣ ክትትሉን መቀጠል
3- ከፍተኛ የደም ማነስ ካለ እና የፅንሱ እድገት በቂ ከሆነ ቶሎ በኦፕሬሽን ማዋለድ 
4- የፅንሱ እድገት ገና ከሆነ በአደጉ አገራት ማህፀን ውስጥ እያለ ደም ሊሰጠውና እድገቱ አስተማማኝ እስከሚሆን ጠብቆ ማዋለድ 


በተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ክሊኒካችን ቀርበው የማህፀን ስፔሻሊስታችንን ዶ/ር ኑሩን ማግኘት ይችላሉ።
አድራሻችን - ኮተቤ ወረዳ 13 ወሰን ግሮሰሪ አካባቢ ያገኙናል ፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0944-72-44-44 ወይም 0930-03-13-17 ይደውሉ ።